-46-777-0614 info@sptc.edu.et Sawla, Gofa Zone, Ethiopia
🇬🇧 English 🇪🇹 አማርኛ

የሳዉላ ፖሊቴክንክ ኮሌጅ ድረ-ገጽ በይፋ ተመረቀ


የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ፣ ተማሪዎች እና የስራ አጋሮቻችን በሙሉ፡
በዛሬው ቀን ማለትም በቀን 14/9/2018 ዓ.ም የተቋማችንን ሁለንተናዊ አገልግሎትና መረጃዎች ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግረው ይፋዊ የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ድረ-ገጽ (Website) በታላቅ ድምቀት መመረቁን ስናበስር በላቀ ደስታ ነው!
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ድረ-ገጽ የተቋሙ ዋና ዲን፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናና ኢንተርፕራይዞች ልማት አሰልጣኝነት ስራ ሂደት (ቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ/ስ ሂደት) እና ምክትል ዲን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም መላው አሰልጣኞች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
ይህ ዲጂታል መድረክ የተቋማችንን መረጃዎች፣ ስልጠናዎችና አገልግሎቶች በአንድ ቦታ በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል በመሆኑ፣ መላው የኮሌጃችን ተማሪዎች፣ ሰልጣኞች እና ባለድርሻ አካላት ድረ-ገጹን ጎብኝታችሁ ጠቃሚ መረጃዎችን እንድትወስዱና እንድትጠቀሙበት በታላቅ አክብሮት እንጋብዛለን።
የቴክኖሎጂ መጋቢው የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ! ? ድረ-ገጻችንን አሁኑኑ ይጎብኙ!