Innovations & Technologies

Technology Image
General Mechanics

የኤሌክትሪክ ምጣድ!

በሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቀረበ አዲስ የኤሌክትሪክ ምጣድ! ለተከበራችሁ የሳውላ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ፤ የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የፈጠራ ስራዎችን በማበረታታት ለህዝባችን የዕለት ተዕለት ኑሮ መቃለል ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። አሁን ደግሞ በአገር በቀል ዕውቀትና በቀላሉ በአካባቢያችን በሚገኙ የጊቢ ዕቃዎች (Recycled Materials) የተሰራ ድንቅ የኤሌክትሪክ ምጣድ ለናንተ አቅርቧል።

Technology Image
General Mechanics

የበቆሎ መፈልፈያ ማሽኖች

የበቆሎ አምራች አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች የምስራች! የበቆሎ ምርትዎን በሰው ኃይል ለመፈልፈል የሚፈጅብዎትን ድካምና ጊዜ የሚያስቀሩ፣ በኮሌጃችን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተሰሩ ዘመናዊ የበቆሎ መፈልፈያ ማሽኖች ለሽያጭ ቀርበዋል።

Technology Image
it

የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኦንላይን ምዘና ስርዓት (Online Assessment System) አበልጽጎ ስራ ጀመረ!

ኮሌጃችን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያደርገው ጥረት፣ የተማሪዎችን ምዘና (Assessment) ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ዲጂታላይዝድ የሚያደርግ የውስጥ ሶፍትዌር ስርዓት ስራ ላይ ውሏል። ይህ ቴክኖሎጂ ምን ለውጥ ያመጣል? ፈጣን ውጤት (Instant Feedback): ተማሪዎች ፈተናውን እንደጨረሱ ወዲያውኑ ውጤታቸውን እንዲያውቁ በማድረግ ረጅም የጥበቃ ጊዜን ያስቀራል። ከወረቀት ንክኪ ነፃ (Paperless System): ለፈተና የሚወጣውን ከፍተኛ የወረቀትና የህትመት ወጪ በመቀነስ የአካባቢ ጥበቃንና የኮሌጁን ሀብት ይቆጥባል። ፍትሃዊነትና ግልጽነት: አውቶማቲክ በሆነ የማረሚያ ዘዴ (Auto-grading) ስለሚሰራ፣ የአድልዎ ወይም የመሳሳት ዕድሎችን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል። ከፍተኛ ጥበቃ (Secure Environment): እያንዳንዱ ተማሪ የራሱ የሆነ የመግቢያ ኮድ (Login) ያለው ሲሆን፣ የፈተና ጥያቄዎች እንዳይሾልኩና እንዳይጭበረበሩ በከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታጠረ ነው።