Latest News
News
የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የክላስተር ኮሌጆች የቴክኖሎጂና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር እና የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡
(ሳውላ፣ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም)
ሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከክላስተር ኮሌጆች ጋር በመተባበር “በቴክኖሎጂ እንቅደም ወደ ስኬት እንድረስ” በሚል መሪ ቃል ያዘ...
(ሳውላ፣ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም)
ሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከክላስተር ኮሌጆች ጋር በመተባበር “በቴክኖሎጂ እንቅደም ወደ ስኬት እንድረስ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የቴክኖሎጂና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር እና የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን በደማቅ ሁኔታ ተካሂዶ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ጊንዳ ባህሩ በንግግራቸው እንደገለጹት፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዋና ተልዕኮ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ማፍራት፣ ተግባራዊ የምርምር ውጤቶችን ማመንጨት እና ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ ፈጠራዎችን ማበረታታት በመሆኑ፣ ይህ ውድድርና ኤግዚቢሽን የኮሌጆችን የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳየትና የልምድ ልውውጥን ለማጠናከር አስፈላጊ መድረክ መሆኑን ገልጸው ፕሮግራሙን በይፋ ከፍተዋል።
የፕሮግራሙ ዓላማ በክላስተር ኮሌጆች ውስጥ የሚገኙ አሠልጣኞች፣ ተማሪዎች እና ኢንተርፕራይዞች ያፈሯቸውን ፈጠራዊ ቴክኖሎጂዎች፣ ተግባራዊ የምርምር ውጤቶች እና ችግር ፈቺ ሥራዎችን ለማስተዋወቅ፣ የልምድ ልውውጥን ለማጎልበት እና የፈጠራ ባህልን ለማጠናከር ነበር።
በውድድሩ እና ኤግዚቢሽኑ ላይ ከተለያዩ ክላስተር ኮሌጆች የቀረቡ ቴክኖሎጂዎች እና የምርምር ሥራዎች በዳኞች በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት ተገምግመው አሸናፊዎች ተለይተዋል። የቀረቡት ሥራዎች የቴክኖሎጂ ፈጠራን፣ ተግባራዊነትን እና ለማህበረሰቡ ችግር መፍትሔ የመስጠት አቅማቸውን በግልጽ ሁኔታ አሳይተዋል።
በመዝጊያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ እና የኮሌጁ ምክትል ዲን ተወካይ አቶ መሳይ ባህሩ ባደረጉት ንግግር፣ በፕሮግራሙ የታዩ ፈጠራዎችና የምርምር ውጤቶች የኮሌጆችን እየተሻሻለ የመጣ የቴክኖሎጂ አቅም እንደሚያሳዩ ገልጸው፣ ወደፊትም ተቋማት በጋራ በመሥራት ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በማፍራትና ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ለፕሮግራሙ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ ክላስተር ኮሌጆች፣ አሠልጣኞች፣ ዳኞች፣ አጋር አካላት እና የኮሌጁ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበው ፕሮግራሙን በይፋ ዘግተዋል።
Website: https://www.sptc.edu.et/
Facebook: Sawla Polytechnic
News
ሳውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ ISO 21001:2025 የትምህርት ተቋማት አስተዳደር ስርዓት (EOMS) ትግበራ ጉዞው ውስጥ የውስጥ ኦዲት (Internal Audit) ስልጠናን በተሳካ ሁኔታ በቀን 5/10/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ
June 12,2026 Sawla Polytechnic College is proud to announce the successful completion of the Interna...
June 12,2026 Sawla Polytechnic College is proud to announce the successful completion of the Internal Audit Training phase in our journey toward implementing the ISO 21001:2025 Educational Organizations Management System (EOMS).
Following Gap Analysis, Implementation Manual Training, and Document Preparation Training, our task forces have now completed Internal Audit Training delivered by experts from the Institute of Ethiopian Standards. We are now preparing for the final stage of the certification journey the External (Third-Party) Audit.
We extend our sincere appreciation to the Institute of Ethiopian Standards, our management team, management representatives, task forces, and all staff members who have contributed to this important initiative.
This progress reflects our commitment to quality education, institutional excellence, stakeholder satisfaction, and continuous improvement.
ሳውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ ISO 21001:2025 የትምህርት ተቋማት አስተዳደር ስርዓት (EOMS) ትግበራ ጉዞው ውስጥ የውስጥ ኦዲት (Internal Audit) ስልጠናን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን በደስታ ያበስራል።
ከGap Analysis፣ በES ISO 21001:2018 የልማትና ትግበራ መመሪያ ስልጠና እና የሰነድ ዝግጅት ስልጠና በኋላ፣ የኮሌጁ የስራ ኃይሎች (Task Forces) በኢትዮጵያ ስታንዳርድስ ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች የተሰጠውን የውስጥ ኦዲት ስልጠና በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ኮሌጃችን ወደ መጨረሻው የማረጋገጫ ሂደት ማለትም የውጭ (Third-Party) ኦዲት ለመግባት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።
ለዚህ አስፈላጊ ተግባር የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የኢትዮጵያ ስታንዳርድስ ኢንስቲትዩት፣ የኮሌጁ አመራር፣ የአስተዳደር ተወካዮች፣ የስራ ኃይሎች እና ሁሉም ሰራተኞች ከልብ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
የዚህ ስራ ዉጤት ጥራት ላለው ትምህርት፣ ተቋማዊ ልቀት፣ የባለድርሻ አካላት እርካታ እና ቀጣይነት ላለው መሻሻል ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል።
#SawlaPolytechnicCollege #ISO21001 #EOMS #QualityEducation #InstitutionalExcellence #ContinuousImprovement
News
የሳዉላ ፖሊቴክንክ ኮሌጅ ድረ-ገጽ በይፋ ተመረቀ
የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ፣ ተማሪዎች እና የስራ አጋሮቻችን በሙሉ፡
በዛሬው ቀን ማለትም በቀን 14/9/2018 ዓ.ም የተቋማችንን ሁለንተናዊ አገልግ...
የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ፣ ተማሪዎች እና የስራ አጋሮቻችን በሙሉ፡
በዛሬው ቀን ማለትም በቀን 14/9/2018 ዓ.ም የተቋማችንን ሁለንተናዊ አገልግሎትና መረጃዎች ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግረው ይፋዊ የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ድረ-ገጽ (Website) በታላቅ ድምቀት መመረቁን ስናበስር በላቀ ደስታ ነው!
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ድረ-ገጽ የተቋሙ ዋና ዲን፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናና ኢንተርፕራይዞች ልማት አሰልጣኝነት ስራ ሂደት (ቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ/ስ ሂደት) እና ምክትል ዲን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም መላው አሰልጣኞች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
ይህ ዲጂታል መድረክ የተቋማችንን መረጃዎች፣ ስልጠናዎችና አገልግሎቶች በአንድ ቦታ በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል በመሆኑ፣ መላው የኮሌጃችን ተማሪዎች፣ ሰልጣኞች እና ባለድርሻ አካላት ድረ-ገጹን ጎብኝታችሁ ጠቃሚ መረጃዎችን እንድትወስዱና እንድትጠቀሙበት በታላቅ አክብሮት እንጋብዛለን።
የቴክኖሎጂ መጋቢው የሳውላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ! 🌐 ድረ-ገጻችንን አሁኑኑ ይጎብኙ!